በግብጽ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ።

በአረብ ዓለም እጅግ እየተዛመተ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን ለመግታት ሀገራት ትምህርት ቤቶችን ፣ ምግብ ቤቶችን ዘግተዋል፡፡

አለም አቀፍ በረራዎችንም ከመጋቢት ወር ጀምረው ሰርዘዋል፡፡

ወረርሽኙ የግብፅን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በእጅጎም ጉድቶታል፡፡

ሀገሪቱ በክረምቱ ወቅት ቱሪስቶችን ለመቀበል እንደምትችል ተስፋ አድርጋለች፡፡

አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎቿንም ከሀምሌ 1 ጀምሮ ለመክፈት አቅዳለች፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በትናንትናው እለት እንዳሳወቁት በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግብጻዊያን 50 ሺህ 437 ደርሷል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 938ቱ ህይወታቸው አልፏል፡፡

የአገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በሰኔ 1 ላይ ባወጣው አንድ ጥናት በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው አምስት እጥፍ ሊበልጥ ይችላል ብሏል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *