ባልፈጸሙት ወንጀል ለ24 አመት በእስር የቆዩት ወንድማማቾች የ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ካሳ ተሰጣቸው።

ባልፈጸሙት ወንጀል ለ24 አመት በስር የቆዩት የአሜሪካ ባልቲሞር ግዛት ወንድማማቾች የ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንደተሰጣቸው ተነግሯል ።

ሁለቱ ወንድማማቾች ባልፈጸሙት የነብስ ማጥፍት ወንጀል ተከሰው ለ24 አመት ለእስር ቢቆዩም አቃቢ ህግ ባደረገው ዳግም ምርመራ የወንጀል መርማሪዎች የፈጸሙትን ስህተት ተረድቶ ወንድማማቾቹ ባሳለፍነው ግንቦት ከእስር ተፈተዋል ።

የሁለቱ ወንድማማቾች ጉዳይ በአሜሪካ ብሄራዊ ውይይት በማድረግ የፖሊስ እና የፍትሕ ስርዓት እንዲሻሻል አግዟል ተብሏል ።

ሁለቱ ጥቁር ወንድማማቾች በፈረንጆቹ 1994 ወንጀሉ በተፈጸመበት ቦታ አለመገኝታቸው ተረጋግጧል ።

የ21 አመት ወጣት ገድለዋል ተብለው ዘብጥያ በወረዱበት ወቅት የእነሱም እድሜ በ20ዎቹ መጀመሪያ እንደነበር ተነግሯል ።

Innocence Project የተባለ ድርጅትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው ፣ በግዛቲቱ በነጻ መሰናበት የሚገባቸው 30 ፍርደኞች ሲኖሩ ሁለቱ ወንድማማቾች ደግሞ ካሳ የተከፈላቸው ዘጠነኛ እና አስረኛ ሰዎች ናቸው ተብሏል ።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.