የፈረንሣይ የዜና ወኪል የመንግስታቱን ድርጅት ሪፖርት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ አሜሪካ እና ቻይና ለዓለማችን የማዕድን ምድር በሚል ለምትታወቀው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጦር በድብቅ ጦር መሳሪያይረዱ ነበር ተብሏል።
ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የቀረበው ሚስጥራዊ ሪፖርት የጦር ኃይሎች እና ስልጠና ለኮንጎ ጦር ኃይል የሚሰጡ አገራት እንዳሉ ተነግሯል፡፡
በድርጅቱ አሰራር መሰረት ማንኛውም አገር ለሌሎች አገራት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ሲያደርግ ለተባበሩት መንግስታት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይሁንና ለዲሞክራቲክ ኮንጎ ጦር የጦር መሳሪያ ድጋፍ ያደረጉት እነዚህ አገራት ለመንግስታቱ ድርጅት አለማሳወቃቸው በዚያች አገር አለመረጋጋት ድጋፉ ሚና ሳይኖረው አይቀርም ተብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች በሰኔ ወር ማብቂያ ላይ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት ምን አይነት ለውጦችን አምጥተው እንደሆነ ይገመግማል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም











