ኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት ለኮቪድ-19 ህሙማን ለመጠቀም ወሰነች።

የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት “ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡”

የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድኝገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል” ብለዋል።

ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ እንደሚወጣም ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *