የምዕራብ አፍሪካ አገራት ድንበሮቻቸውን በቅርቡ እንደሚከፍቱ አስታወቁ።

በኮቪድ 19 ምክንያት ድንበሮቻቸውን ዘግተው የቆዩት የምዕራብ አፍሪካ አገራት አሁን ላይ ለመክፈት አስበናል ነው ያሉት፡፡

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህረሰብ አገራት /ECOWAS ሚኒስትሮቹ ቀጠናው የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀምር እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

በቀጠናው ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ9 መቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይዎታቸው አልፏል፡፡

የፋይረሱን ሥርጭት ተከትሎ የቀጠናው አገራት የትራንስፖርት ዕገዳ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ከዚህ ወር ጀምሮ ድንበራቸውን እንደሚከፍቱ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የየብስ ትራንስፖርት እና የአገር ውስጥ የአውሮኘላን በረራ በቅርቡ አገልገሎት መስጠት ይጀምራሉ ነው የተባለው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.