ሰበር ዜና :-ግብፅ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በማቋረጥ በድጋሚ ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት መውሰዷን አስታወቀች።

ያለ ሶስቱ ሃገራት ስምምነት ኢትዮጵያ በተናጥላዊ ውሳኔ ግድቡን ውሃ መሙላት ሳትጀምር የፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ በኩል መጠየቋን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ግብፅ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን ለመውሰዷ ምክንያት ያደረገችው እየተካሄደ የሚገኘው የውሀ ሚንስትሮች የሶስትዮሽ ውይይት አዎንታዊ ውጤት ስለማያመጣ መሆኑን ሚንስትሩ ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በተናጥል ውሀ መያዝ እንዳትች የፀጥታው ምክር ቤት እንዲያስቆምላት መጠየቋ ተገልጿል።

ግብጽ ከአንድ ወር በፊት ለጸጥታው ምክር ቤት ተመሳሳይ ደብዳቤ ለጽጥታው ምክር ቤት ማስገባቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያም ለግብጽ መልስ በላከችው ደብዳቤ ለጸጥታው ምክር ቤት በራሴ ተፈጥሯዊ ወንዝ የማንንም ፈቃድ አልጠይቅም ውሀውን መጠቀሜንም እቀጥላለሁ ማለቷም አይዘነጋም።

በዚህም ምክንያት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽ ጉዳዩን በሶስትዮሽ ድርድር እንድትፈታ ጫና ማሳደሩን ተከትሎ ወደ ድርድሩ ተመልሳ ነበር።ይሁንና የተጀመረው የሶስቱ አገራት የውሀ ሚንስትሮች ውይይት ሳይጠናቀቅ ግብጽ በድጋሚ ድርድሩን ማቋረጧን አስታውቃለች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ

ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *