ብሔራዊ ሎተሪ በየ አስራ አምስት ቀኑ ያወጣ የነበረውን የመደበኛ ሎተሪ እጣ አቋረጠ፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር 600 ሺህ ብር ደርሶ የነበረው የመደበኛ ሎተሪ እጣ አስተዳደሩ በደረሰበት ኪሳራ ምክንያት እጣው እንዲቋረጥ መወሰኑን ገልጿል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የመደበኛ ሎተሪ የሎተሪ ሺያጭ በ30 በመቶ እንደቀነሰበትም ነው አስተዳደሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገረው፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ ንዋይ እንደተናገሩት ባጭር ጊዜ ሎተሪው ተሸጦ ካላለቀ ከፍተኛ ኪሳራ ነው የሚያጋጥመው ያ ደግሞ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲታይ የማይፈቻል ነው ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና አስተዳድር ባለፉት 11 ወራት ከሎተሪ ሽያጭ 702 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

አስተዳደሩ አስራ አምስት አይነት የሎተሪ አይነቶችን ለገበያ አቅርቦ ነው ይህንን ብር የሰበሰበው፡፡

ይህም የእቅዱን 83 ከመቶ ጠቅላላ የገበያ አፈጻጸም እንደሆነም ነው ያስታወቀው፡፡

አስተዳደሩ በበጀት አመቱ በጠቅላለው 143 ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን 278 ሚሊየን ብር ለባለ እድለኞች እንዲሁም 111 ሚሊየን ብር ደግሞ ለሎተሪ አዟሪዎች ኮሚሽን እንደከፈለም ገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *