ከሩዋንዳ ወደ አትላስ የሚወስደው መንገድ በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰየመ።

የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

በመርሀግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተዋል።

ጀነራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።

የመታሰቢያ መርሀግብሩ እየተከናወነ ያለውም በዚህ ቦታ ላይ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ጀነራል ሰዓረ ህይወታቸው ሲያልፍ ቦታው ላይ ፓርክ ለማሰራት ይፋ ባደረገው መሰረት የመታሰቢያ ፓርክ ግንባታው በይፋ ተጀምሯል።

ከሩዋንዳ ወደ አትላስ የሚወስደው መንገድም በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰይሟል።

በመታሰቢያ መርሀግብሩ ላይ የጀነራል ሰዓረ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም የተለያዩ አመራሮች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.