ሳውዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ መካ የሚደረገው የሀጂ ጉዞ ላይ እገዳ ጣለች፡፡

ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ የሚያደርጉት የሀጂ ጉዞ ላይ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

ዘንድሮው በመካ የሚካሄደው ሀይማኖታዊ የፀሎት ስነ ስርዓትም ጥቂት የሀገሬው ዜጎች ብቻ የሚታደሙበት ይሆናል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡

ዘንድሮ በመካ የሚደረገው ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓትም ከነጭራሹ ሊሰረዝ ይችላል የሚሉ ስጋቶችም እንዳሉ ተነግሯል፡፡

የከሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባይከሰት ኖሮ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ወደ መካ እና መዲና ያቀኑ ነበር ተብሏል፡፡

በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ወደ መካ የሚደረገው ይህ ሀይማኖታዊ ጉዞ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ዘንድሮ ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሀገሪቱ ዜጎች ብቻ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን ይታደማሉ፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣትም አካላዊ እርቀትን ለማስጠበቅ እና የሰዎችን ደህነት ለማረጋገጥ ብቸኛው አማራጭ ጉዞውን ማገድ ስለነበር ይህንኑ አድርገናል ብለዋል፡፡

በሳውድ አረቢያ ከ 161 ሺ በላይ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 1 ሺ 307 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.