በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ።

አደጋው የደረሰው በትናትናው ዕለት ሲሆን በታራሚዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል።

አደጋው በትላንትናው ዕለት ከረፋዱ 5፡30 ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የአባላት መኖርያ ካምፕ የእሳት ቃጠሎ ደርሶ ነበር፡፡

በማረምያ ቤቱ በደረሰው የእሳት አደጋም በህግ ታራሚዎች ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ነው ማረሚያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡

ነገር ግን በእሳት አዳጋው ምክንያት በካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አባላት ንብረታቸው ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ቃጠሎው የተነሳበት ቦታም ታራሚዎች ከሚገኙበት ግቢ ውጪ ያለ ቦታ በመሆኑ ከህግ ታራሚዎች ጋር የሚያገኛኘው ነገር እንደሌለም ማረሚያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ቃጠሎው በአካካቢው ማህበረሰብ እና በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ርብርብ በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

የንብረት ጉዳት እና መኖሪያቸው ለተቃጠለባቸው አባላት ሌላ ማረፊያ ቦታ የተዘጋጀ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.