በግብጽ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፉ የሕክምና ዶክተሮች ቁጥር 91 ደረሰ።

እንደ አገሪቱ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ከሆነ በግብጽ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስካሁን 91 ዶክተሮች ህይወታቸው አልፏል።

የግብጽ የዶክተሮች ማህበር መንግስት አሁንም በፊት አውራሪነት ቫይረሱን እየተዋጉ ላሉት የህክምና ሰዎች ትኩረት አልሰጠም ሲል እየከሰሰ ነው፡፡

በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 55 ሺህ 233 ሲደርስ 2 ሺህ 193 ሰዎች ደግሞ ህይወታው አልፏል፡፡

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ በእጅጉ እየተፈተነች ያለችው ሌላኛዋ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ነች፡፡

እስካሁን በሀገሪቱ 101 ሺህ 590 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 1 ሺህ 991 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር እንዳለው በየቀኑ የመመርመር አቅሜን አሁን ወደ 25 ሺህ አድርሻለሁ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥም 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎቼን መርምሪያለሁ ብሏል፡፡

በወረሽኙ የሚሙቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 2 ነጥብ 2 በመቶ መጨመሩን ያስታወቀው ሚኒስትሩ የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር 53 ሺህ 444 ደርሷል።

ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ናይጂሪያ 21 ሺህ ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከዚህ ውስጥ 7 ሺህ 109 ያሉ አገግመዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 9 ሚሊየን 209 ሲደርስ 474 ሺህ 797 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 4 ሚሊየን 956 ሺህ 983 ደርሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *