አቶ ሳንዱካን ደበበ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ ሳንዱካን ደበበ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ ሳንዱካን ወደዚህ ሃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።

በአቶ ሳንዱካን ቦታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ደግሞ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ መሾማቸውን ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ከአንድ አመት በላይ የመሩት አቶ አበበ አበባየሁ ከቀናት በፊት በራሳቸው ፈቃድ ሃላፊነት መልቀቃቸው ይታወሳል።

የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሀላፊ በነበሩት ሌሊሴ ነሜ አቶ አበባውን ተክተው መሾማቸው ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *