ኢራን የኒኩሌር ማመንጫ ማዕከሏን በአዲስ መልክ ማደሷ ተነገረ።

ቴህራን የቡሽር የኒኩሌር ማመንጫ ተቋሟን በራሷ ሳይንቲስቶች አማካኝነት ማደሷ ተነግሯል ፡፡

የአገሪቱ የአቶሚክ ኢንርጂ ድርጅት እንዳስታወቀው የመጀመሪያው የኒኩሌር ተቋም የሆነውን የቡሽር ማዕከል ጥገና ተደርጎለት በአዲስ መልክ ሥራ ይጀምራል ብሏል፡፡

ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በሩሲያ አማካኝነት የተገነባ ሲሆን አሁን ላይ ግን በራሷ ሳይንቲስቶች እንደታደሰ ታውቋል፡፡

የቡሸር የኒኩሌር ቀጠና ለመጀመሪያ ጊዜ አመታዊ የነዳጅ መለዋወጫና የጥገና ማዕከል እንዳዳለውም ተነግሯል ፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ሬዛ ባናዝዴህ ሲናገሩ ውስብስብ የሆነውን ሥራ በራሳችን ኤክስፐርቶች መስራታችን ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡

ይህም ኢራን ከሩሲያ ድጋፍ ተላቃ በራሷ ባለሙያዎች ማንቀሳቀስ እንድትችል ይረዳታል ነው የተባለው፡፡

የኒኩሌር ማዕከሉ 1 ሺህ ሜጋ ዋት እንደሚያመነጭ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይም ቴህራን 20 ሺህ ሜጋ ዋት የሚያመንጭ ተቋም እገነባለሁ ብላለች፡፡

ለዚህም 100 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ሲል የዘገበው ፕሬስ ቴሌቪዥን ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *