የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራን ለማቆም የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢዝነስ አማራጮቹን በመጠቀም ላይ መሆኑን አስታውቋል።

በአየር መንገዱ የካርጎና ሎጀስቲክስ ማነኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ፍፁም አባዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኮሮና ፈተናዎችን ለመቋቋም ፊቱን ወደ ካርጎ ጭነት አገልግሎት ማዞሩን ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ፊቱን ወደ ካርጎ ባዞረበት ወቅት እርሱን ማስተናገድ የሚችሉ የጭነት አውሮፕላኖች ቁጥር 12 ብቻ የነበረ መሆኑን አቶ ፍፁም አንስተዋል፡፡

በወቅቱ የነበረውን ፍላጎት ለማጣጣም ተጨማሪ 24 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወንበር ነቅሎ ወደ ስራ ማስገባቱን ይናገራሉ፡፡

አየር መንገዱ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ ካርጎ የመቀየሩን ሂደት የውስጥ ሰራተኞቹን እውቀቶች በመጠቀም ያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ ለካርጎ ጭነት አገልግሎት ብቻ በአጠቃላይ 36 አውሮፕላኖችን አሰማርቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር ግን መንገደኞችንና ጭነትን በጋራ የሚያስተናግዱ አውሮፕላኖችም ስራ ላይ እንደነበሩ ዳይሬክተሩ ነግራናል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህክምና ቁሳቁሶችን በማሰራጨት እረገድ እንደ ቀይ መስቀል አለምን አንዳስተናገደ አቶ ፍፁም ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ከሰጠባቸው መካከልም አፍሪካ ፤ አውሮፓ ፤ ኤሺያንና ደቡብ አሜሪካን አገራት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

አቶ ፍፁም አሁን ላይ አየር መንገዱ ለ29 የአፍሪካ ሀገራት በቋሚነት የካርጎ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ቋሚ ባልሆነ መልኩ ለ52 የሀጉሪቱ ሀገራት ተደራሽ ሆኗል ብለዋል፡፡

የአለም የአቬሽን ኢንደስትሪ አንገቱን በደፋበት በዚህ ወቅት የአየር መንገዱ ገቢ ምን ይመስላል የሚል ጥያቄ ሰንዝረናል፡፡

አቶ ፍፁም እንዳሉት በኢትዮጵያ ሰኔ መጨረሻ በጀት አመቱ የሚዘጋ በመሆኑ አየር መንገዱ ከካርጎ ብቻ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ያገኛል ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢዝነስ አማራጮቹን በአግባቡ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አንስተዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎችን ለማቆም መገደዱን ተከትሎ ለገጠመው ችግር አማራጭ የቢዝነስ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን ገቢ በበጀት ዓመቱ መገባደጃ አንደሚያሳካው ነግረውናል፡፡

በኮቪድ-19 ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ዝግ ሆነው መሰንበታቸው ይታወቃል፡፡
አሁን አሁን አንዳንዶቹ አየር መንገዶቻቸውን ወደ ስራ እያስገቡ ይገኛል፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ አየር መንገድም ነገሮች ወደ ቀድሞ ሲመለሱ አውሮፕላኖቹን ለመንገደኞች ዝግጁ ይደረጋሉ ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.