መንግስት ለ2013 ካቀረበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ የ126 ቢሊዮን ብር ጉድለት አጋጥሞታል።

የፌደራል መንግስት ለ2013 በጀት ዓመት 476 ቢሊዮን ብር የበጀት ረቂቅ ማቅረቡ ይታወሳል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በዛሬው ውሎው በዚህ እና በሌሎች ጀንዳዎች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴዕታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በዚህ ጊዜ እንዳሉት መንግሥት ለ2013 በጀት ዓመት 476 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ቀርቧል።

ከዚህ ረቂቅ በጀት ውስጥ 271 ቢሊዮን ብሩን ከታክስ ለማሟላት የታቀደ ሲሆን በአጠቃላይ 126 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ይኖረዋል።

ዶክተር ኢዮብ እንዳሉት ያጋጠመውን የበጀት ጉድለት እንዴት ሊሸፈን እንደታሰበ ለምክር ቤቱ አባላት አብራርተዋል።

በዚህም መሰረት 48 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ከውጭ ከሚገኝ እርዳታና ብድር፣ 77 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከአገር ውስጥ ብድር ለመሸፈን መታቀዱን ተናግረዋል።

ይህንን የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ከቀረቡት መፍትሄዎች ውስጥ በአገር ውስጥ ብድር የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት የቀረበው መፍትሄ የምርቶች ዋጋ ግሽበትን አያመጣም ወይ? የሚል ጥያቄ ከምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል።

የአገር ውስጥ ብድርን ከግምጃ ቤት ሽያጭና ከብሔራዊ ባንክ በመበደር ለመሙላት እቅድ መያዙን እና ይህ መሆኑ ደግሞ የኑሮ ውድነትን እንደማያመጣ ዶክተር ኢዮብ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ እና ሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን መለዋወጥ በሚያስችላት ስምምነት ዙሪያ እና በሌሎች 13 አጀንዳዎች ዙሪያ እየተወያየ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *