በፓኪስታን ካሉ አብራሪዎች ውስጥ 30 በመቶዎቹ የአብራሪነት ፈቃድ የላቸውም ተባለ።

262 የሚጠጉ የፓኪስታን ፓይለቶች የአብራሪነት ፍቃድ እንደሌላቸው የአገሪቱ ትራንስፖርት ሚንስትር ተናገረዋል።

በፓኪስታን ከሶስት ፓይለቶች አንዱ የአብራሪነት ፍቃድ እንደሌላቸው ተገልጿል።

የፓኪስታን የአቬየሽን ሚኒስትር እንደተናገሩት በሀገራቸው ተቀጥረው ከሚሰሩ ፓይለቶች በርካቶቹ የአብራሪነት ፍቃድ የላቸውም ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለሀገራቸው ፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት 30 ከመቶ የሚሆኑ ፓይለቶች የአብራሪነት ፍቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ፓይለቶቹ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናም እንዳልወሰዱ የተገለጸ ሲሆን በፈተና ወቅት ከፍተኛ ገንዘብ በመክፍል ሌላ ሰው እንዲፈተንላቸው ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡

ከነዚህ ውስጥም በርካቶቹ ምንም የአብራሪነት ስልጠና ያልወሰዱና የትኛውም የበረራ ልምድም የሌላቸው ናቸው ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በፓኪስታን በአቬየሽን መስርያ ቤት እውቅና የተሰጣቸው ባጠቃላይ 860 ፓይለቶች እንዳሉም ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ከሰሞኑ በሀገሪቱ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ 97 ዜጎች ሂወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *