የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ራሳቸውን ለሁለት ሳምንት አግለዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ይህንን ያደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር መገናኘታቸው ከታወቀ በኃላ ነው።

ፕሬዝዳንቱ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ ቢሆኑም ለማንኛውም በሚል ነው ለሁለት ሳምንት ያህል ራሳቸውን አግለው ለማቆየት የወሰኑት ብሏል ጽ/ቤታቸው፡፡

ቢቢሲ አፍሪቃ እንዳለው የሴኔጋሌ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዬያ ዶዲያሉ በትናንትናው ዕለት በቫይረሱ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሰዎች ንፅህናን መጠበቅ እና ማህበራዊ መዘናጋትን መቀነስ የመሳሰሉ አስፈላጊ የግል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ሴኔጋል እስካሁን ድረስ 93 ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ 6 ሺህ 129 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.