የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ዛሬ ረፋድ ተመርቆ በይፋ ስራውን ጀምሯል።
ዳቦ ፋብሪካው በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ለማከፋፈያ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።
የፋብሪካው ግንባታ በ9 ወራት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ዳቦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ ይሆናል።
400 የሚሆኑ የአንበሳ አውቶብሶችም እድሳት ተደርጎላቸው ለመሸጫነት እንዲውሉ በየአካባቢው ተዘጋጅተዋል።
ዳቦዎችን ለተጠቃሚዎች እንዲያደርሱ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶች ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም











