የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ካርቱም ገቡ።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ሱዳን ካርቱም ያቀኑት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ጋር በሁለቱ አገራት እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር እንደሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ አስታውቋል።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት በሱዳኑ አቻቸው ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ግብዣ እንደሆነም ተገልጿል።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኦስማን ሳሌህ እና አማካሪያቸውን የማነ ገብረአብን አስከትለው ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *