ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የጣናን ህልውና ለመታደግ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

በአማራ ክልል የሚገኙ ስድስት ዩንቨርሲቲዎች ጣናን ለመታደግ የፍቅርና የትብብር ጉዞ ወደጉና ተራራ በማድረግ በዛሬው ዕለት ችግኝ ተክለዋል፡፡

የደብረ ታቦር ዪንቨርሲቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የሀይቁን ህልውና ለመጠበቅ እና ተፋሰሶችን ለማልመት ስምምነት ተደርሷል ብሏል፡፡

የደብረታቦር ዪንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ የጉና ተፈጥሮ ሀብት ለመጠበቅ የስድስቱም ዪንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው ዕለት ተተክለዋል ብለዋል፡፡

እነዚህም ዩንቨርሲቲዎች የደብረ ታቦር የጎንደር የባህረዳር የደበረ ማርቆስ የደባርቅ እና እንጂባራ ናቸው፡፡

ጣናን ከሚገብሩ ተፋሰሶች መካከል 50 በመቶ የሚጠጋውን የሚሸፍነው የጉና ተራራ እንደሆነ የገለፁት ዶክተር አነጋግረኝ ሀይቁን ለመንከባከብ ተፋሰሶችነ ማልመት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የጣናን ሀይቅ ከእንቦጭ በተጨማሪ ወደ ሀይቁ የሚገባው አፈር እና ደለል ለችግር እንደዳረገውም አንስተዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመግባቢያ ሰነድ በጉና ተረራ ላይ መፈራረማቸው ታውቋል፡፡

በቀጣይም በሌሎች የአካባቢ ጥበቃ እና የምርምር ስራዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

የጣና ሀይቅ በእንቦጭ ከተወረረ ከ8 አመት በላይ ቢያስቆጥሩም እስካሁን ግን ዘላቂ መፍትሄ አለማግኘቱ ይታወቃል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.