በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ት/ቤት አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን በፌደራል ፖሊሶች እና በዘራፊዎች መካከል ለደቂቃዎች የቆየ ተኩስ ልውውጥ ተፈጥሮ ነበር ተባለ።

ከተኩስ ልውውጡ በኋላ ካፒታል ጋዜጣ በቦታው በመገኘት እንደዘገበው በጥይት ተመቶት የወደቀ ሆኖም በሸራ የተሸፈነ ሰው ይታይ ነበር፡፡

እንዲሁም አንድ ግለሰብ መሬት ላይ ተኝቶ ማየት የተቻለ ሲሆን ግለሰቡ እንቅስቃሴ ያሳይ እንደነበር ከርቀት ለመታዘብ ችያለሁ ብሏል።

በአካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ለጋዜጣው እንዳረጋገጡት የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከዝርፊያ ጋር የሚገናኝ ነው፡፡

በዘራፊነት የተጠረጠሩት ግለሰቦችም የፌደራል ፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ለወንጀል የተሰማሩ የነበሩ ሆኖም አባል ያልሆኑ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የአይን እማኞች እንደገለፁት የተኩስ ልውውጡ ከሁለቱም ወገን ማለትም ከፀጥታ አካላት እንዲሁም ተጠርጥረው ከሚያመልጡት ወገን እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ለማምለጥ ጥረት እያደረጉ እንደነበር የገለፁት የአይን እማኞች መኪናዋ በጥይት ተመትታ ትዛዝ ሆቴል የሚባል አካባቢ ቆማ ትገኛለች፡፡

በአካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳዩ ገና በመጣራት ላይ ያለ ነው ማለታቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 19 ቀን 2012 .ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.