ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ እንስት ሐኪም በአሜሪካ የcovid-19 ጽኑ ህሙማንን አገግመው እንዲወጡ ሳትታክት በሰራችው ስራ በኒዮርክ ከተማ የክብር እውቅና ተሰጣት።

ትውልደ ኢትዮጲያዊቷ አሜሪካዊት በአሜሪካን አሉ ከሚባሉ 10 ሆስፒታሎች መካከል አንዱ በሆነውና በኒዮርክ ከተማ በሚገኘው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ በቀዶ ህክምና ሀኪምነት (Surgeon) በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

ዶ/ር ምስክር እሸቱ አባተ በዓለማችን የተከሰተውን የcovid-19 ወረርሽኝ ለመከላከል በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ በጽኑ ህሙማን ክፍል (intensive care unit – ICU) ለህሙማን በተዘጋጀ የማናፈሻ ማሽን በመታገዝ መተንፈሻ አካል በሆነው ሳንባ ውስጥ የመተንፈሻ ቱቦ በጥበብና በጥንቃቄ እያስገባች ለበርካቶች የሞት ጣር እፎይታ መሆን ችላለች፡፡

እንዲሁም ለህሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄና እንክብካቤ በማድረጓ እሷ የምትከታተላቸው ህሙማን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አገግመው ከሆስፒታሉ ሊወጡ ችለዋል።

ከዚህ የተነሳ በርካታ አሜረካዊያንን ከሞት በመታደጓ በአሜሪካን አገር የተመረቀችበት ኮንኮርዲያ ፕሪስቲጂየስ ዩኒቨርሲቲ ለታታሪዋ ዶ/ር ምስክር እሸቱ አባተ ላበረከተችው እጅግ በጣም የላቀ ስራ የዓመቱ ጀግኒት በማለት የክብር እውቅና ሰጥቷታል።

ላበረከትችው አስደናቂ ስራ ክብር ደግሞ በኒዮርክ ከተማ ምስሏን በትልቅ ቢልቦርድ ሰቅሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.