ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፋሬድሪክሰን የአውሮፓ ህብረት መሪዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርኝን በተመለከት በተዘጋጀ ጉባሄ ላይ ለመገኝት የጋብቻብ ቀናቸውን መሰረዛቸው ተነግሯል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዳሉት የአውሮፓ አባል ሀገራት መሪዎች በፊታችን ሐምሌ 17 እና 18 2020 ከኮሮና ወረርሽኝ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ የገጽ ለገጽ ውይይት ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ በመያዙ ከሰርጌ ቀን ጋር ተጋጭቷል ብለዋል ።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች በሚካሄዱት ውይይት ላይ የኮቪድ 19 የማገገሚያ ፈንድ እና አዲስ በጀት ላይ ምክረ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሎ እንድሚጠበም ተነግሯል ።
በአውሮፓ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቀውስ ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን ዋስትና ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት የዴንማርክን ጥቅም የሚነካ ከሆነ ግን እንደማይተባበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ተናግረዋል ።
ጠቅላይ ሚንስትሯ በጋብቻ ለመጣመር ቀነ ቀጠሮው የተሰረዘበት እጮኛቸውን ይቅርታ ስለታገስክኝም አመሰግናለሁ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም











