የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የደህነት አማካሪ ጆን ቦለተን ያሳተሙትን አዲሱ መጽሀፍ በቻይና ተሞካሸ፡፡

የቀድሞ የአሜሪካ የደህንነት ሀላፊ የነበሩት ጆን ቦልተን ከሰሞኑ አዲስ መጽሀፍ አሳትመዋል፡፡

ታድያ ይህንን መጽሀፍ ነው በቻይና ዘንድ አድናቆት የተቸረው፡፡

አዲሱ የጆን ቦልተን መጽሀፍ በወቅታዊ የሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ የገባችውን የፖለቲካ ሽኩቻ እንዲሁም ከቻይና ጋርም ስለ ተፈጠረው የንግድ ግጭት እና ሌሎችም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መጽሀፍ ነው ተብሏል፡፡

በመጽሀፉ በዋናነት የተካተተው ግን የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ያለበትን የአስተዳደር ክፍተት እና ከሌሎች ሀገራት ጋር የፈጠሩት የዲፕሎማሲ ክፍተት የሚያሳይ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

ጆን ቦልተን የፕሬዝዳንት ትራምፕን አስተዳደር የኮነኑበት ዋነኛው ጉዳይ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ላይ በወሰዱት ደካማ የሆነ ምላሽ ነው ይላል የሲኤን ኤን ዘገባ፡፡

በመጀመርያ ፕሬዝዳንቱ ቫይረሱን መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ ሲገባቸው ቫይረሱ ከተነሳበት ሀገር ጋር ቁርሾ መግባት አልነበረባቸውም ይህ ደግሞ ሀገርን ከመክዳት እና የግል ሀሳብን ከማንጸባረቅ ጋር ይገናኛል ብለዋል ጆን ቦልተን በመጽሀፋቸው፡፡

ይህ ጉዳይ ነው በዋናነት በቻይና ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው፡፡

አሜሪካ ከቫይረሱ አመጣጥ ጋር በተያያዘ ቻይናን የምትከስበት ምንም አይነት ማስረጃ የላትም በመሆኑም የትራምፕ አስተዳደር ቻይናን ከመውቀሳቸው በፊት የጆን ቦልተንን መጽሀፍ ያንብቡ ብለዋል የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዛዎ ቻይ።

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ መጽሀፍ እንዳይታተም ለማሳገድ ቢሞክሩም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጽሀፉ ለህትመት በቅቶ አሁን በመነበብ ላይ ይገኛል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.