20 ሚሊዮን አሜሪካዊያን በኮሮና ቫይረስ ሳይጠቁ እንዳልቀረ የአሜሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር አስታወቀ።

የሀገሪቱ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከላዊ መሥሪያ ቤት (CDC) እንደሚለው እውነተኛው ቁጥር አሁን ከሚነገረው በ10 እጥፍ ሊጨምር ይችላል፡፡

እናም በተቀመጠው ግምት መሰረት በአሜሪካ በዚህ ጊዜ 20 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል ማለት ነው፡፡

መረጃው የተገኘው የቴክሳስ ግዛት ከቅርብ ቀናት ወዲህ በሆስፒታሎች ያሉ አልጋዎች መሙላታቸውን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ ማላላቱን ለጊዜው እንዲቆይ መወሰኗን ተከትሉ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ መንግስት እያለ ያለው እስካሁን 2.4 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል 122 ሺህ 370 ሰዎች ደግ ህይወታቸው አልፏል ነው፡፡

የተወሰኑ የደቡብ እና ምዕራብ ግዛቶች የእንቅስቃሴ ገደብን ማላላታቸውን ተከትሎ የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡

የዋሺንግተን ዩኒቨርስቲ የሟቾች ቁጥር በመጭው ጥቅምት ወር 180 ሺህ ይደርሳል ሲል የተነበየ ሲሆን ምናልባት አሜሪካዊያን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በሥነ ሥርዓት መጠቀም ከጀመሩ ግን የሟቾች ቁጥር በጥቅምት መጨረሻ 146 ሺህ ብቻ ይሆናል ብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.