የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተያዙ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሆነ ነው።


ዛሬ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እሰከጫኑበት ክሬን እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች የመብራት ኃይል ሰራተኞች ነን በሚል ማጭበርበሪያ ከመስሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ህብረተሰቡ በሚጠቀምበት የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ ስለሆነ ህብረተሰቡ ለኤሌክትሪክ ኃይል ንብረቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ ተጠቆመ፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁ.1 በሚባል አካባቢ ሠኔ 19/2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፤30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመስሪያ ቤቱ ዕውቅና ውጭ ኮድ3ኢ.ት84535 በሆነ ክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪ ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ም/ዳይሬክቶሬት የሆኑት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ለአዲስ ፖሊስ ገልዋል፡፡
ግለሰቦቹ በኃላፊያቸው ታዘው ትራንስፎርመር ለመቀየር መምጣታቸውን ቢናገሩም በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሰርሞሎ ግለሰቦቹን መሥሪያ ቤቱ እንደማያውቃቸውና ከመሥሪያ ቤቱ የታዘዙ ቢሆኑ እንኳን የትዕዛዝ ደብዳቤ መያዝ እንደነበረባቸው ገልጸው ለማነኛውም ትዕዛዝ ሰጥቶናል እንድንሰራ ያሉትንም ሓላፊ ከፖሊስ ጋር በጋራ እንደሚያጣሩት በበኩላቸው አስረድተዋል ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን ለመቀጠል ተጠርጣሪዎቹንና በእግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶችን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን የገለጹት ኮማንደር ያሲን ሁሴን በመብራትና በሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ህ/ተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና የመብራት ኃይል ሰራተኞች ነን በሚል የሚመጡ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህጋዊ ሰራተኞች ስለመሆናች በአግባቡ ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#መረጃው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.