በኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት ዘጠኝ አዳዲስ እና ግዙፍ የመስኖ ልማት ግድቦችን ለመገንባት መታቀዱን የመስኖ ኮሚሽን አስታወቀ።

የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በ2013 በጀት ዓመት 9 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል፡፡

የመስኖ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሚካኤል መሀሪ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በ2013 በጀት ዓመት 9 አዳዲስ እና ትላልቅ የመስኖ ልማት ግድብ የመገንባት ፕሮጀክት መታቀዱ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም 3 የጥገና ፕሮጀክት እና 10 የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ጥናት እና ዲዛይን ፕሮጀክቶችን ለመጀመርም ታቅዷል፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር ሚካኤል መሀሪ እንዳሉን በቀጣይ ዓመት የሚጀመሩት አዳዲስ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች አንገር ፣ገላና፣ግልገል አባይ፣ዳቡስ፣የሽንሌ ከርሰ ምድር ውሀ ፣አላይ ደጌ ፣ኬጦ እና ወይቦ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ሲሆኑ የመገጭ የመስኖ አውታር ስራም በዚህ ውስጥ ተካቷል ብለዋል፡፡

ፈንታሌ እና ቆቦ ቂላና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የጥገና ፕሮጀክት መያዙንም ኮሚሽነሩ ነግረውናል፡፡

በአጠቃላይ በ2013 የሚጀመሩት የመስኖ ግድብ ልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከ132 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያለማሉ ተብሎም ይታሰባል፡፡

132 ሺ ሄክታር መሬት ያለማሉ ተብሎ የሚታሰቡት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የ2013 በጀት ዓመት እቅድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ እቀዱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ከኮሚሽነሩ ሰምተናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *