ጋና ለጤና ሰራተኞች አድርጋው የነበረውን የታክስ ቅነሳ ለተጨማሪ ሶስት ወራት አራዘመች።

የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ-አድዶ ትላንት በቲሌቪዝን በተላለፈው መግለጫቸው ለጤና ሰራተኞች ተደርጎ የነበረው ማበረታቻ ለተጨማሪ ሶስት ወራት መራዘሙን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት በዋናው ደመወዛቸው ላይ የ 50 በመቶ ጭማሪ ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ እንዲሁም በሐምሌ ፣ ነሐሴ እና መስከረም ወራትም የገቢ ግብር አይከፍሉም ፡፡

ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮናቫይረስ ታማሚ ካገኘች ጀምሮ ለጤና ባለሙያዎቿ የተለያዩ ማበረታዎችን ላለፉት ሶስት ወራት ስታድርግ ነበር ፡፡

ፕሬዝዳንቱ አኩፎ አድዶ ትላንት ምሽት ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት ማበረታቻዎቹ የበሽታው ወረርሽኝ በሀገሪቱ መከሰቱን ተከትሉ ውጊያውን በፊት አውራሪነት የሚዋጉትን የጤና ባለሞዎችን ለማነቃቃት በማሰብ የተጀመረ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ጋና እስካሁን 17 ሺህ ያህል ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ስታረጋግጥ 112 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

ባለፊት ሶስት ወራት በጋና 294 ሺህ 867 ምርመራዎችን ተካሄደዋል፡፡

በአህጉሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ምርመራን ካደረጉት ውስጥ አንዷ ናት ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

በሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ ጥላው የነበረውን ገደቦች ያነሳች ሲሆን ትምህርት ቤቶችም ዳግም ቢከፈቱም ድንበሮቿ አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *