ቻይና በኮንግ ኮንግ የመገንጠል እንቅስቃሴን ሲያራምዱ ነበር ያለቻቸዉን አራት ተማሪዎች አሰረች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በቻይና የረቀቀዉና ብዙ እያወዛገበ የሚገኘዉ አዲሱ የብሄራዊ ደህንነት ማስጠበቂያ ህግ፣የቻይናን አንድነት አደጋ ዉስጥ የሚከት ማንኛዉምን መረጃ ማሰራጨት ይከለክላል፡፡ አዋጁ ታዲያ በተለይም ሆን ኮንግ ነዋሪዎች ላይ ያነጣተረ ነዉ በሚል ትችትና ተቃዉሞ ሲያስተናግድ ቢቆይም ቻይና ህጉን መተግበር ጀምራለች፡፡ በዚህም አራት ተማሪዎች የሆንግ ኮንግን የመገንጠል ሃሳብ በማህበራዊ ሚዲያ ሲያራምዱ ነበር በሚል ማሰሯን አስታዉቃለች፡፡ ተማሪዎቹ ቀደም ሲልም በዚህ ህግ […]

ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝተናል ብለዋል። ከትርፉ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግብር ከፍያለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 318 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር እዳንም ከፍያለሁ ብሏል። እንደ ወ/ት ፍሬህይወት የተገኘው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር […]

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተጨማሪ አራት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሮና ቫይረስ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ተጨማሪ የኮቪድ ምርመራ ማዕከላት ለመክፈት ማሰቡን ቢሮው አስታውቋል። የቢሮው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዋሌ በላይነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የአማራ ክልል በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ከሆኑ ክልሎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁንም በሰምንት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከላት እስከ ትናንት ድረስ 28 ሺህ 621 ናሙናዎች የመረመረ ሲሆን 504 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው […]

አሜሪካ 12 ሽህ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ ነዉ መሆኑን አስታዉቃለች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

አሜሪካ ይህን እርምጃ የምትወስደዉ ጀርመን ለኔቶ የሚጠበቅባትን ያህል መዋጮ እየከፈለች አይደለም በሚል ነዉ ተብሏል፡፡ የትራምፕ አስተዳደር እንዳለዉ በቀጣይም፣ ከጣሊያንና ቤልጅየም 6 ሽህ 4 መቶ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ ይደረጋል ብሏል፡፡ ትራምፕ በትናንትናዉ አለት ባሰሙት ንግግር ከዚህ በኋላ ስለ ኔቶ የገንዘብ መዋጮ ከአዉሮፓ ሀገራት ጋር የምንከራከርበት ምክንያት የለንም፤ቀላሉ መፍትሄ የወታደሮቻችንን ቁጥር እንቀንሳለን ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የክፍያ […]

ኢትዮጵያ በቀጣዩ በጀት ዓመት 18 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ መሆኗ ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም አጠቃላይ ስራዎችን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። እንደ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ ኢትዮጵያ ለ2013/14 የምርት ዘመን 18 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት የጨረታ ሰነድ እየተዘጋጀ ነው። ኢትዮጵያ በ2012/13 የበልግ እና የመኸር ግብርና ስራዎች 17 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከህንድ ፣ሞሮኮ፣ቻይና፣ግብጽ እና ከተባበሩት አረብ ሂሚሬቶች መግዛቷ […]

ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ በኦላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ በኦላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች ስልጠና በአዲስ አበባ በመስጠት ላይ ይገኛል። የዩንቨርሲቲ መግቢያ ወይም የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመወሰድ ስልጠኛው ላይ የተሳፉ አይነ ስውራን ተማሪዎችም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት […]

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነው ሃይድሮ ክሎሮከውን ለኮኖና ቫይረስ ህክምና እንዲያገለግል እየተከራከሩ ነው፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ፕሬዘደንቱ ይህ የጸረ ወባ መድሃኒት አሁንም ቢሆን ከኮሮና ቫይረስ የተሻለ ማገገሚያ ነው በማለት በሃገሪቱ ከሚገኙ የጤና ባለሙዎች ጋር ክርክር መግጠማቸውን CNN ዘግቧል፡፡ ለምን አታምኑኝም ይህ የዋባ መድሃኒት ለኮኖና ቫይረስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ለዚህም እኔን እንደ ማሳያ ልትወስዱኝ ትችላላችሁ ብለዋል ትራምፕ። ይሁን አንጂ ከ አንድ ወር በፊት የሃገሪቱ የምግብና የአደንዛዥ እፅ ተቋም መድኃኒቱ ከወባ ህመምተኞች ውጪ […]

ፌስቡክ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለአፍሪካ ቴሌኮም መሰረተ ልማት 57 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ኩባንያው በ57 ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካን የቴሌኮም መሠረተ ልማት ችግር ለመፍታት ወጪ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የኩባንያው የምስራቅ አፍሪካ ፅህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ 5 አመታት የአፍሪካን የቴሌኮም መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት እሰራለሁ ብሏል፡፡ እንደ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ከ800 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከበይነ መረብ ጋር ያልተሳሰሩ […]

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ ከማምረት አቅሙ በግማሽ በመቶ ቀንሶ ዳቦ እያመረተ መሆኑን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በተመጣጠነ ዋጋ ዳቦ ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ እንዲችል ታስቦበት ሥራ የጀመረው ይህ ፋብሪካ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ ያመርታል በሚል ነበር፡፡ ባለፈው ሰኔ ወር ተመርቆ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ የሚገኘው ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት የታሰበውን ያክል እያመረተ ይሆን? ስንል ጠይቀናል። የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ ቡልቡላ እንደነገሩን ፋብሪካው በሰዓት 80 ሺህ የማምረት አቅም ቢኖርም በአሁኑ ሰዓት እያመረተ ያለው ግን በሰዓት […]

የኮሮና ቫይረስ 90 በመቶ በላይ ሽፋን ያገኘው በከተሞች ላይ ብቻ መሆኑን ተመድ አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ዓለም ከፍተኛ የጤና ቀውስ እንዳይከሰት መስራት እንዳለባትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሳሰቡን ሲጂቲኤን ዘግቧል። ድርጅቱ እንዳለው በአለማችን ላይ ኮሮና ቫይረስ እያስከተለ ካለው ከፍተኛ ጉዳት ባሻገር ተጨማሪ የጤና ቀውስ እንዳይከሰት የየሃገራት መሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በተለይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ኑሮ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለው ጉዳት ምንም ትኩረት […]