ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት ከ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧ ተገለጸ።


በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም በሩን በመዝጋቱ ምክንያት የዓለም ኢንቨስትመንት ማሽቆልቆሉ ይታወሳል።
የሰዎች እንቅስቃሴ መገደብ፣የንግድ መቀዛቀዝ እና የኢኮኖሚ መላሸቅ ለዓለማችን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መቀነስ ትልቁ ምክንያት ነው።
በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እቅድ ይዛ የነበረችው ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር መሳቧ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስታወቀው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ስራው እስከ ጥር የካቲት ወር ድረስ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነበር።
ይሁንና ከመጋቢት ወር ጀምሮ ግን በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተቀዛቅዟል ብሏል።
ኢትዮጵያ በ2011 በጀት ዓመት 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧ አይዘነጋም።
በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 6 ሺህ የሚጠጉ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመጡ የውጭ አገራት ኩባንያዎች በስራ ላይ ሲሆኑ የሀይል እጥረት ችግር እንዳለባቸው ይገልጻሉ።
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አምሰት ዓመታት በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለ290 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ማቀዷን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሰምተናል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *