ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን ሲያደርጉት የነበረው ድርድር መቋረጡ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ላለፉት 11 ቀናት ሲካሄድ እንደነበር ይታወሳል።

በድርድሩ ላይ የሶስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች፣የቴክኒክ ባለሙያዎች እና 11 ታዛቢዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነበር።

ይሁንና ይህ የሶሰትዮሽ ድርድር ባሳለፍነዉ ሰኞ ምሽት ካለስምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ሶስቱም ሀገራት የዉይይቱን ሪፖርት በዛሬዉ እለት ለአፍሪካ ህብረት እንደሚያቀርቡም ነዉ ተገለጸዉ፡፡

ከዚሁ ከህዳሴዉ ግድብ ጉዳይ ሳንወጣም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዉሃ መያዝ መጀመሩ ተገልጧል፡፡

በአዉሮፓ ሳተላይት ኤጀንሲ ከተነሱ ምስሎት ይህን ተረድቻለሁ ብሎ አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበዉ ግድቡ ዉሃ መያዝ ጀምሯል፡፡

ካፒታል ጋዜጣም ኢትዮጲያ ባሳለፈነው እሮብ የመጀመሪያን ዙር የአባይ ግድብ ውሀ ሙሌት መጀመሯንና ለተወሰኑ ሳምንታትም ግድቡን ውሀ የመሙላት ሂደት እንደሚቀጥል መዘገቡን መንገራችን ይታወሳል፡፡

ይሁንና በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ግን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ይፋዊ መግለጫ እስካሁን አልተሰጠም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክርተር አበይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የግድቡ ውሀ ሙሌት በያዝነው የክረምት ወር አለማስጀመር የማይታሰብ ነው ብለው ነበር፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *