ከኮሮና ባይረስ የሚያገግሙ ሰዎች ባይረሱን ሊያስተላልፍ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ተነገረ፡፡


ከሰሞኑ በሃገራችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝ መበራከቱን ተከትሎ አሃዙ እንዴት ከፍ ሊል ቻለ ሲል ኢትዮ ኤፍኤም ጠይቋል፡፡
የሚሊኒየም ማገገሚያ ማእከል ዋና ዳሬክተር ዶ/ር እስማኤል ሸምሰዲን እንደነገሩን ከሆነ
ሳይንስ እንዳረጋገጠው አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው በውስጡ ህይወት ያለው ቫይረስ ከ 8 ወይንም ከ 9 ቀናት በኋላ ወደ ቅንጣትነት ያለው ባይረስ እንደሚቀየር ነው፡፡
ታዲያ ይህ ቅንጣት ወደ ሌሎች የማስተላለፍ አቅሙ ደካማና ቫይረሱም ህይወት ያለው ቫይረስ እንዳልሆነ ነው፡፡
ታዲያ ይህን ግኝት ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ከ 10 ቀናት በኋላ ሰዎች ይህ ቅንጣት ቫይረስ ቢታይባቸውም ወደየመኖሪያ ቤታቸው ቢለቀቁ ችግር እንደማይኖረው ወይንም የማስተላለፍ እድላቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ነው፡፡
ይሁን እንጂ ከየማገገሚያ ማእከላቱ አገግመው ወደ የመኖሪያ ቤታቸው እዲያቀኑ የሚደረጉት ግለሰቦች ባይረሱን የማስተላለፍ አቅማቸው እጅግ ዝቅተኛ ቢሆንም ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ አያስተላልፍም የሚል ጥናት በሳይንስ ባለመረጋገጡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸውም ነው ዶ/ር ኢስማኤል የነገሩን ፡
ምንም እንኳን ቫይረሱ ከገሮሮ ላይ ቢጠራው በሰገራ ላይ የመቆየት እድል ስላለው ይሄ ከፍተኛ ጥንቃቄና ክትትል እንደሚያስፈልግም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *