የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት የግድቡን ተፈጥሯዊ የግንባታ ሂደት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለኢትቪ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አሁን ላይ ግድቡን በተመለከተ በሳተላይት የሚታዩ ምስሎች ትክክለኛ መሆናቸውንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።

ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውን ትውልድ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልከ የሚደረግ እንደሆነ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ጨምሮ ከኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ማዳጋስካር እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 11 ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *