ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ሙሉ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር መሆኑን የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን ለመስጠት ያልተቻለበት ሁኔታ በመፈጠሩ አስገዳጅ ከሆኑ ማስረጃዎች ውጪ የፓስፖርት አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም፡፡

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር ሳኦል ጣፋ እንደነገሩን ምንም እንኳን የፓስፖርት አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በተቋሙ የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ መቆየቱን አንስተው ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ አስገዳጅ ጉዞ ለሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ አካላት ሲሰጥ መቆየቱን ነግረውናል፡፡

የትምህርት፤የጤና፤የስራና የሌሎችም አስገዳጅ ጉዞዎች ብቻ የፓስፓርት አገልግሎትን በመስጠት ላይ የሚገኘው ተቋሙ በቀጣይ ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን መስጠት የሚያስፈልግበት ሁኔታ በመፈጠሩ በቅርቡ በሙሉ አቅም ወደ ሰራ ለመግባት መታቀዱን ነግረውናል፡፡

ተቋሙ በትናንትናው ዕለት ከ2 ሺህ በላይ ችግኞችን በሱሉልታ አቅራቢያ ባለ አንድ ተራራማ ቦታ ላይ ተክሏል።

በየውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.