ኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት ከ340 ሺህ በላይ የተሸከርካሪ ሰሌዳ ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባቷ ተገለጸ፡፡

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳስታወቀው በ2012 በጀት ዓመት ከ340 ሺ በላይ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ከውጪ ማስገባታቸውን ነግረውናል፡፡

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ማለትም በ2011 ወደ 220 ሺ የተሸከርካሪ ሰሌዳን ከ ውጪ በውጪ ምንዛሬ በማስገባት ለትራንስፖርት ቢሮዎች መከፋፈሉን የነገሩን የተቋሙ የሰሌዳና ምልክቶች ምርትና ስርጭት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ገዛኘኝ ግራባ ናቸው፡፡

ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ 9 ኮኒቲነር የተሸከርካሪ ሰሌዳዎቹን ከውጪ ለማስገባት ከ85 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማደረጉን የነገሩን አቶ ገዛኘኝ ሰሌዳዎቹን በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንቅፋት መሆኑን ነግረውናል፡፡

ኢትዮጲያ የተሸከርካሪ ሰሌዳን ከጀርመን ሃገር የምታስገባ ሲሆን ይህም ሃገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ የውጪ ምንዛሬን እንድታወጣ እያደረጋት ይገኛል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *