የአዲስ አበባ ትራስፖርት ቢሮ መመሪያ በተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣት 14 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በበጀት ዓመቱ 36 ሺ 124 የትራፊክ መመሪያ የመተላለፍ ጥፋቶች የተመዘገበ ሲሆን በነዚሁ ጥፋተኞች ላይ በተወሰደ እርምጃም 14 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።

የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ለጣቢያችን እንዳሉት 36ሺ 124 ጥፋቶች በመዲናዋ ባሉ የኮድ 1 ፣ የኮድ 3 ታክሲ ፣ ሸገር ፣አንበሳ እና ሀይገር ባስን ጨምሮ ባሉ አሽከርካሪዎች ላይ የተከሰቱ የህግ መተላፎች መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

አሽከርካሪዎቹ ካጠፉት ጥፋቶቹ መከላከልም ከተፈቀደው በላይ ትርፍ የጫኑ፣ ከተፈቀዱ ቦታዎች ውጪ መኪና ያቆሙ እና የተለያዩ የትራፋክ ህጎችን ተላልፈው የተገኙ አሽከርካሪዎች መሆናቸውንም አቶ አረጋዊ ነግረውናል፡፡

ቢሮው ከዚህ በተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ የተላለፉ ከ10 ሺ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቋል።

ከመጋቢት አስከ ሰኔ መጨረሻ ባሉት 4 ወራት ውስጥ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የወጣውን የትራስፖርት ስርዓት መመሪያ ተላልፈው በተገኙ 10ሺ 450 አሽከርካዎች ላይ አርምጃ ተወስዷል፡፡

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.