ቻይና በቼንግዱ የሚገኝውን የአሜሪካን ቆንስላ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሰጠች፡፡

እንደ CNN ዘገባ ሀገሪቷ ቆንስላውን እንዲዘጋ ትዕዛዝ ያስተላለፈችው አሜሪካ በሂውስተን የሚገኝውን የቻይና ቆንስላ መዝጋቷን ተከትሎ ነው፡፡

ቻይና አሜሪካ የወሰደችው እርምጃን ተከትሎ አጸፋውን እመልሳለሁ ማለቷ ይታወሳል፡፡

አሜሪካ የቻይና ቆንስላ ለመዝጋት የወሰነችው የሀገሪቷን አእምራዊ ንብረት ለመጠበቅ ሲል እንደሆነ አስታውቆ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በቻይና መንግስት ድጋፍ የሚደረግላቸው ቻይናዊያን በኮሮና ቫይረስ ምርምር ላይ ስርቆት ፈጽመዋል በማለት ነበር ቆንስላውን የዘጋችው፡፡

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር በንግድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል።

አሜሪካ ቆንስላውን መዝጋቷን ተከትሎ ቻይና በወቅቱ ሀገሪቷ የፈጸመችው ድርጊት አለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ያሻከረ ድርጊት ብላው ነበር፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *