ሀይሌ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ መኪና ስጦታ አበረከተ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኤሌክትሪክ ኃይል አማካኝነት የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተቀብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሀዩንዳይ ፕሬዚደንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርቦን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ይህን በኢትዮጵያ የተገጣጠመ መኪና ለየት የሚያደርገው፣ የተለየ የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን ለመሙላት መቻሉ ነው።

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.