በቻይና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከሀገሪቱ መውጣት ጀምረዋል፡፡

ቻይና በቼን-ግዱ የሚገኝው የአሜሪካ ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው ዲፕሎማቶቹ ከሀገሪቷ መውጣት የጀመሩት፡፡

ሀገሪቷ ቆንሱሉን እንዲዘጋ ትዛዝ ያስተላለፈችው፣ አሜሪካ በሂውስተን የሚገኝውን የቻይና ቆንሱል መዝጋቷን ተከትሎ ነው፡፡

ዲፕሎማቶቹ በቼንግዱ የአሜሪካ ቆንስል ቅጥር ግቢ ለቀው ሲወጡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል፡፡

በቼንግዱ የሚገኙ ያካባቢው ነዋሪዎችም ፣ዲፕሎማቶቹ አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በግል ስልካቸው ፎቶ ሲነሱም እንደነበረ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር፣ በንግድ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል።

አሜሪካ ቆንሱሉን መዝጋቷን ተከትሎ፣ ቻይና በወቅቱ ሀገሪቷ የፈጸመችው ድርጊት አለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ያሻከረ ድርጊት ነዉ ማለቷ ይታወሳል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.