አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም መቸገሩን የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ካን ጋሏክ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋምቤላ ክልል እየተመዘገበ ያለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እለት ተእለት እያሻቀበ መሆኑን ነው፡፡

ወረርሽኙን ማህበረሰቡ አቅልሎታል የሚሉት ካን ማህራዊ እርቀትን ያለመጠበቅ ፤ኮሮና እንደ ጉንፋን ስለሆነ ይዞ ይለቀናል በሚል የተዛባ አመለካከትና የመዝናኛ በተለይም የምሽት ክበባት እርቀትንም ሆነ ቫይረሱን ለመከላከል በማያመች መንገድ ወደ ስራ መግባት ለችግሩ መባባስ ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

የፀጥታ አካላት ማህበራዊ ተልኳቸውን ለመወጣት በከፍተኛ ሁኔታ መቸገራቸውንና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም ጥረት በሚደረግበት ወቅት አንዳንድ አካላት ከ ፀጥታ አካላት ጋር እስከመጋጨት የሚደርሱበት አጋጣሚ መኖሩንም ሃላፊው አታውቀዋል፡፡

ወረርሽኑ እያደረሰ ካለው ጉዳት ባሻገር ማህበረሰቡ ለቫይረሱ ያለው ግንዛቤ መላላት ዋጋ እንዳያስከፍልም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግም ነግረውናል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *