እንደ ካዛብላንካ፣ታንጋየር፣ማራካሽ፣ፌዝ እና ሜክኔስ ባሉ የሀገሪቱ ትልልቅ ከተሞች እንቅስቃሴዎች መታገዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እገዳው የማይመለከታቸው በመንግስት ባለስልጣናት ፍቃድ ያገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቻ ናቸው፡፡
እንደ ባለስልጣናቱ በነዚህ ትልልቅ ከተሞች በድጋሚ ከቤት ያለመውጣት መመርያ የተላለፈው የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጣው መመርያ ባለመከበሩ ነው፡፡
ዜጎች መመርያውን አለማክበራቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ እገዳውን ሀገር አቀፍ እንደሚያደርው የሞሮኮ መንግስት አስጠንቅቋል፡፡
በሞሮኮ ቅዳሜ 811፣ እሁድ ደግሞ 633 ሰዎች በእያንዳንዱ ቀን የተያዙ ሲሆን ባጠቃላይ የተያዘው ሰው 20 ሺህ 278 ደርሷል፡፡
በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም











