በዓለማችን ከትቢ በመቀጠል ሁለተኛው ገዳይ የሆነው የጉበት በሽታ ቀን በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ከጉበት በሽታ ነጻ የሆነ ነገን እንፍጠር በሚል መሪ ቃል በአለም ለ10ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በአለም ላይ በጥቅሉ ወደ 325 ሚሊየን የሚሆነው ህዝብ በሄፓታይተስ እድሜ ዘለቅ የጉበት ኢንፌክሽን ተጠቂ ሲሆን ወደ 257 ሚሊየን በሄፓታይተስ ቢ እና 71 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ በሄፓታይተስ ሲ ተጠቂ ናቸው፡፡

በየአመቱ 1.3ሚሊየን የሚገመት ህዝብ በሔፓታይተስ ምክንያት ለሞት እንደሚዳረግም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

ይህም ከቲቢ በመቀጠል በአለም ላይ ሁለተኛ ለሞት የሚዳርግ ገዳይ በሽታ ያደርገዋል፡፡

ከኤች አይቪ ጋር ሲወዳደር በኤች አይቪ ከሚያዘው ሰው ይልቅ በሄፓታይተስ የሚያዘው ሰው ቁጥር በዘጠኝ እጥፍ ይበልጣል፡፡

ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት እና በኢስያ የሄፓታይተስ በሽታ በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡

በሀገራችን በፈረንጆቹ 2017 በተሰራ አንድ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በሽታው በስፋት ተሰራጭቶ ከሚገኝባቸው ሀገራት መካከል ስትሆን እስከ 10 ሚሊየን ሰው በሄፓታይተስ ቢ እና 3.5ሚሊየን ሰው ደግሞ በሄፓታይተስ ሲ የተጠቁ ናቸው ተብላል፡፡

የሄፓታይተስ ሲን በህክምና ማዳን የሚቻል ሲሆን ሄፓታይተስ ቢን ደግሞ በህክምና ቫይረሱ በመቆጣጠር የኢንፌክሽን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ማድረግ እንደሚቻል ነው የተነገረው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *