ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የፊታችን ሰኞ ሊሰበሰቡ ነው፡፡

የሱዳኑ የሙሃና መስኖ ሚንስቴር እንዳለዉ ህብረቱ ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ ሶስቱን ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ለሶስት ቀናት እንዲወያዩ ይደረጋል ማለታቸውን የፈረንሳዩ አጃንስ ፍራንስ ዘግቧል፡፡

ዉይይቱ በአፍሪካ ህብረት ስር የሚካሄድ ሆኖ የደቡብ አፍሪካዉ ፕሬዝዳንት ስሪል ራማፎሳ ይመሩታል ተብሏል፡፡

ይሁንና ዉይይቱ በምን ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ዘገባዉ ያለዉ ነገር የለም፡፡

ሕብረቱ የሶስቱ አገራት መሪዎች በተገኙበት ባካሄደው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ የዉሃ ሙሌቱን መጠናቀቁን ለተሰብሳቢዎቹ በመግለጽ ሰርፕራይዝ ማድረጓ የሚታወስ ነዉ፡፡

የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ደግሞ የግድቡ ውሃ ሙሌት መጠናቀቁ የግብጽን የውሃ ጥቅም እንዳልጎዳው በመዘገብ ላይ ናቸው።

ሶስቱ አገራት በግድቡ በርካታ ጉዳዮች የተግብቡ ቢሆንም በድርቅ ወቅት ሊለቀቅ በሚገባው የውሃ መጠን ላይ ግብጽ ያልተገባ ፍላጎት በማሳየቷ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓም ተገልጽል።

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.