የአሜሪካ ሪፐብሊካን ፓርቲ ከኮቪድ 19 ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማገገም የ1 ትሪሊዮን ዶላር እቅድ አስተዋወቀ፡፡

ሪፐብሊካኑ ኮቪድ 19 በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰውን ኪሳራ ለመካካስ የሚያስችል ተጨማሪ የ1 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ረቂቅ ሀሳብ ማቅረባቸው ነው የተነገረው፡፡

በረቂቅ ሀሳቡ ላይ እንደተቀመጠውም 100 ቢሊየን ዶላር ለትምህርት ቤቶች አንዲሁም ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በነፍስ ወከፍ 1ሺ 200 ዶላር ደግሞ ለሀገሪቱ ዜጎች የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ላይ እንዲውል ሀሳብ ቀርቧል፡፡

በእቅዱ መሠረት በወረርሽኙ ሳቢያ ስራ አጥ ለሆኑ አሜሪካውያን ይከፈል የነበረውን የ600 ዶላር የጥቅማጥቅም ክፍያም እንዲቀንስ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በሪፐብሊካኑ የቀረበው ረቂቅ ሀሳብ ላይ ለስራ አጥ ዜጎች ይከፍል የነበረው የ600 ዶላር የጥቅማጥቅም ክፍያ ወደ 200 ዶላር ዝቅ እንደሚያርውም ነው የተነገረው ፡፡

ይህ ረቂቅ ሀሳብ ለውይይት የቀረበ ሲሆን ከዴሞክራት ፓርቲ አባላት ሀሳቡ ብቁ አይደለም የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡

ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖን ለመቋቋም በሚል እስካሁን 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ ለንግድ ተቋማት እና ለግለሰቦች በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብን የከፈለች ቢሆንም ገንዘቡ ለቀጣዮቹ ጊዜአት ይበልጥ እንደሚስፈልግ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች መተንበያቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *