የጉዞ እገዳን መጣል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ዘላቂ መፍትሄ አይደለም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማገድ ኮቪድ 19ን ለመከላከል ዘላቂ መፍትሄ ስላልሆነ፤ ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ድንበሮቻቸው አካባቢ የታሻሉ ስራዎችን መስራት ይኖርባቸዋል ብሏል፡፡

እንግሊዝ የጉዞ እገዳውን በማንሳት የቱሪዝም ዘርፏን ለጎብኝዎች ክፍት ማድረጓን እና በተለይ ከስፔን የሚሄዱ ጎብኝዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ውሳኔ ማስተላለፏን ሀገራት የጉዞ እገዳውን እያላሉ ስለመሆናቸው በማሳያነትም ጠቅሷል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ኮቪድ 19ን በዘላቂነት ለመከላከል የአፍ እና የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግና አካላዊ እርቀትን መጠበቅ ዋነኞቹ መንገዶች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀነሰ ማለት፤ ቫይረሱ ጠፋ ማለት እንዳልሆነ ከካናዳ ፣ ቻይና ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮሪያ መማር ይገባልም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

ሀገራት ድንበሮቻውን ጥርቅም አድርገው መዝጋታቸውም ተገቢ አይደለም የሚለው ድርጅቱ ፤ሀገራት በኮቪድ 19 የተዳከመውን ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ አካላዊ እርቀትን ባስጠበቀ መልኩ እና አላስፈላጊ የሰዎች ስብስብን በመቀነስ ተንቀሳቅሰው መስራት ይኖርባቸዋል ማለቱን ሮይተረስ ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *