የኮሮና ቫይረስ 90 በመቶ በላይ ሽፋን ያገኘው በከተሞች ላይ ብቻ መሆኑን ተመድ አስታወቀ፡፡

ዓለም ከፍተኛ የጤና ቀውስ እንዳይከሰት መስራት እንዳለባትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሳሰቡን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ድርጅቱ እንዳለው በአለማችን ላይ ኮሮና ቫይረስ እያስከተለ ካለው ከፍተኛ ጉዳት ባሻገር ተጨማሪ የጤና ቀውስ እንዳይከሰት የየሃገራት መሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡

የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በተለይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ኑሮ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለው ጉዳት ምንም ትኩረት አልተሰጠው ሲል ወቅሷል ፡፡

እነዚህ አካባቢዎች ላይ በቂና ንፁህ የመጠጥ ውሃ በአግባቡ ያለመኖር ፤መጠለያና የተለያዩ እክሎች መኖራቸው እየታወቀ እንኳን 90 በመቶ በላይ ስለ ኮሮና ቫይረስ ሽፋን እየተሰጠ ያለው በከተማ ላይ ብቻ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የየሃገራት መንግስታት እራሳቸውን መመልከት አለባቸው ያሉት ጉተሬዝ ይህ ካልሆነ ግን ዓለም ከፍተኛ የጤና ቀውስን ልታስተናግድ እንደምትችል አሳስበዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *