ፌስቡክ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለአፍሪካ ቴሌኮም መሰረተ ልማት 57 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ኩባንያው በ57 ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካን የቴሌኮም መሠረተ ልማት ችግር ለመፍታት ወጪ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የኩባንያው የምስራቅ አፍሪካ ፅህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ 5 አመታት የአፍሪካን የቴሌኮም መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት እሰራለሁ ብሏል፡፡

እንደ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ከ800 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከበይነ መረብ ጋር ያልተሳሰሩ ናቸዉ።

ይህንንም ችግር ለመፍታት በቀጣዮቹ 5 አመታት ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት በትኩረት እንደሚሰራ በመግለጫው አንስቷል ፡፡

ወደፊት ከሚሰሩት ስራዎች መካከልም በባህር ላይ የሚዘረጉ ገመዶች፡በትራንስፖርት እና በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚሠሩ ስራዎች ዋነኞች ናቸው፡፡

በተለይም የ4 እና 5ጂ ኔትዎርኮች በአፍሪካ አገራት ለማስፋፋት እንደሚሰራም ኩባንያው ገልጿል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ዘርፉን ከማስፋፋቱ በተጨማሪ የአፍሪካን ኢኮኖሚ እንደሚያሳድግ በአፍሪካ የኩባንያው የፐብሊክ ፖሊሲ ዳይሬክተር ኮጆ ቦአኪዮ ተናግረዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.