ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነው ሃይድሮ ክሎሮከውን ለኮኖና ቫይረስ ህክምና እንዲያገለግል እየተከራከሩ ነው፡፡

ፕሬዘደንቱ ይህ የጸረ ወባ መድሃኒት አሁንም ቢሆን ከኮሮና ቫይረስ የተሻለ ማገገሚያ ነው በማለት በሃገሪቱ ከሚገኙ የጤና ባለሙዎች ጋር ክርክር መግጠማቸውን CNN ዘግቧል፡፡

ለምን አታምኑኝም ይህ የዋባ መድሃኒት ለኮኖና ቫይረስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ለዚህም እኔን እንደ ማሳያ ልትወስዱኝ ትችላላችሁ ብለዋል ትራምፕ።

ይሁን አንጂ ከ አንድ ወር በፊት የሃገሪቱ የምግብና የአደንዛዥ እፅ ተቋም መድኃኒቱ ከወባ ህመምተኞች ውጪ ሲወሰዱ ከፍተኛ የልብ ህመምን እያስከተለ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ይህ ብቻም ሳይሆን ተያያዥ የጤና እክሎችን እያስከተለ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ይህንን የወባ መድሃኒት በርግጠኝነት ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒትነት እንዲሆን ለማረጋገጥ እንዳልተቻለና ምን አልባትም ገና ብዙ ምርምሮችን እንደሚጠይቅ አስታውቆ ነበር፡፡

ይህ የወባ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና መዋል አለበት ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ነበር ትራምፕ ይፋ ያደረጉት ፡፡

ትራምፕ ዋይት ሃውስ ለሚገኙ ጋዜጠኞች እንዳሉት የሆነ አዲስ ነገር አምጥቼ መፍትሄውን ሳሳያቸው አይ አይሆንም ብቻ ነው መልሳቸው ሲሉ ተችተዋል፡፡

ትራምፕ አክለውም ማንም ሰው ፓለቲካኛ ብቻ ነው ተብሎ ሊደመደም አይገባም ምክንያቱም ስለጉዳዩ ድምዳሜ ለመስጠት ብዙ መፅሃፍትን አገላብጫለሁ ሲሉ በጉዳዩ ላይ እውቀት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ይህ የወባ መድሃኒት ለኮኖና ቫይረስ ዋጋ አለው ያሉት ትራምፕ ከ ትልቁ ልጃቸው ጋር መድሃኒቱ ያለውን ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን የጤና መኮንኖች አረጋግጠዋል በማለት ሰኞ እለት በፌስቡክና በቲውተር ላይ ባጋሩት አጭር ቪዲዮ ከ 17 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሊመለከቱት ችለዋል።

ይህንና ይህንን የፕሬዘዳንቱ ፌስቡክም ሆነ ቲውተር መረጃው የተሳሳተ ነው በሚል ተቋማቱ ሰርዘውታል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *