ቻይና በኮንግ ኮንግ የመገንጠል እንቅስቃሴን ሲያራምዱ ነበር ያለቻቸዉን አራት ተማሪዎች አሰረች፡፡

በቻይና የረቀቀዉና ብዙ እያወዛገበ የሚገኘዉ አዲሱ የብሄራዊ ደህንነት ማስጠበቂያ ህግ፣የቻይናን አንድነት አደጋ ዉስጥ የሚከት ማንኛዉምን መረጃ ማሰራጨት ይከለክላል፡፡

አዋጁ ታዲያ በተለይም ሆን ኮንግ ነዋሪዎች ላይ ያነጣተረ ነዉ በሚል ትችትና ተቃዉሞ ሲያስተናግድ ቢቆይም ቻይና ህጉን መተግበር ጀምራለች፡፡

በዚህም አራት ተማሪዎች የሆንግ ኮንግን የመገንጠል ሃሳብ በማህበራዊ ሚዲያ ሲያራምዱ ነበር በሚል ማሰሯን አስታዉቃለች፡፡

ተማሪዎቹ ቀደም ሲልም በዚህ ህግ መሰረት የታሰሩ ሰዎችን እንደ መቀስቀሻ በመጠቀም የሆንግ ኮንግን ከቻይና የመገንጠል ጉዳይ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲያሰራጩ መቆየታቸዉን ፖሊስ ገልጧል፡፡

ለእስር የተዳረጉ ተማሪዎች ሶስት ወንዶችና አንድ ሴት ሲሆኑ እድሜያቸዉም ከ16 እስከ 21 ዓመት ዉስጥ መሆኑን ሽንግተን ፖስት ጽፏል፡፡

ተማሪዎቹ የመገንጠል እሳቤን ከሚያቀነቅኑ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉን ፖሊስ ደርሸበታለሁ ማለቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.