አሜሪካ 12 ሽህ ወታደሮቿን ከጀርመን ልታስወጣ ነዉ መሆኑን አስታዉቃለች፡፡

አሜሪካ ይህን እርምጃ የምትወስደዉ ጀርመን ለኔቶ የሚጠበቅባትን ያህል መዋጮ እየከፈለች አይደለም በሚል ነዉ ተብሏል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር እንዳለዉ በቀጣይም፣ ከጣሊያንና ቤልጅየም 6 ሽህ 4 መቶ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ ይደረጋል ብሏል፡፡

ትራምፕ በትናንትናዉ አለት ባሰሙት ንግግር ከዚህ በኋላ ስለ ኔቶ የገንዘብ መዋጮ ከአዉሮፓ ሀገራት ጋር የምንከራከርበት ምክንያት የለንም፤ቀላሉ መፍትሄ የወታደሮቻችንን ቁጥር እንቀንሳለን ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የክፍያ ወጭን በአሜሪካ ትክሻ ላይ ብቻ ጭኖ ወዳጅነትንና ደህንነትን ማረጋገጥ አይቻልም ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የትራምፕ ድርጊት ይህ ለሩሲያ ክፍተት የሚፈጥር እርምጃ ነዉ በሚል ተቃዉመዉታል፡፡

የኔቶ አባል ሀገራት ከሚያገኙት ጠቅላላ የሀገር ዉስጥ ምርት ሁለት በመቶ የሚሆነዉን ለኔቶ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸዉ ስምምነቱ ቢያስገድድም ጀርመን ግን ይህን እተወጣች አይደለም በሚል አሜሪካ ትተቻለች፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.